የተለወጠ
መለወጥ [Conversion] አንድ ሰው ኀጢአተኛ መኾኑን አምኖ በመቀበል (ሮሜ 3፥23)፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅነትና የኀጢአት መሥዋዕትነት በማመን (ሮሜ 10፥9)፣ ንስሓ በመግባት፣ ማለትም ከኀጢአታዊ መንገዱ በመመለስ (ሐዋርያት ሥራ 3፥19)፣ በመንፈስ ቅዱስ ርዳታ ዳግመኛ በመወለድ (ዮሐንስ 3፥3-8) ከእግዚአብሔር ጋራ የሚጀምረውን ዐዲስ ሕይወት (2ቆሮንቶስ 5፥17) የሚያመለክት ነው። ይህ ልውጠት የአንድ ወቅት ቅጽበታዊ ኹነት ወይም ውሳኔ ሳይኾን ለዕድሜ ልክ ኢየሱስን የመከተል ውሳኔ ነው (ሉቃስ 9፥23)።



